Teshome Girma Real Estate · Addis Ababa Book a consultation
← ወደ ማውጫው
Local Insight 3 ደቂቃ Read in English

የቅንጦት መስፈርቱ ምንድነው?

አሁን አሁን በአዲስ አበባ ያሉ የሪል እስቴት ድርጅቶች ሁሉ ቤቶቻቸውን «ቅንጡ» ይላሉ። ከቃሉ ጀርባ ሕጋዊ መስፈርት የለም — ስለዚህ የባለሙያ መስፈርት ይኸው፦ ቅንጡ ቤት ስሙን የሚመጥን የኑሮ ልምድ መስጠት አለበት።

አሁን አሁን አብዛኛዎቹ የሪል እስቴት ድርጅቶች የሚገነቧቸውን ቤቶች «ቅንጡ» ወይም "luxury" ብለው ያስተዋውቃሉ። ማንኛውንም ብሮሹር ክፈቱ፣ ማንኛውንም ገጽ ስክሮል አድርጉ — ቃሉ እዚያ አለ፣ በባለ ሁለት መኝታውም በፔንትሃውሱም ላይ። ግን የቅንጦት መስፈርቱ ምንድነው?

ከጀርባው መስፈርት የሌለው ቃል

በእርግጥ ምንም አይነት guide የሚያደርግ በሕግ የተደነገገ መስፈርት በሌለበት ሁኔታ ይሄ ቅንጡ ነው ይሄ ደግሞ አይደለም ማለት ከባድ ሊሆን ይችላል። ቅንጦትን የሚያረጋግጥ ቢሮ የለም። ማንኛውም አልሚ ቃሉን ማተም ይችላል፣ አብዛኞቹም ያደርጉታል። ስለዚህ መለያው ብቻውን ስለ ቤቱ ምንም አይነግራችሁም — ስለ ማርኬቲንጉ ብቻ ነው የሚነግራችሁ።

እኔ ግን እንደ ባለሙያነቴ፣ አንድን ቤት ቅንጡ ነው የምለው የዋጋውን የሮ ተምክሮ ልክ እንደ ስሙ ቅንጡ ማድረግ ሲችል ነው። ፊኒሺንግ አይደለም፣ ሎቢ አይደለም፣ በምልክት ላይ ያለ ቃል አይደለም — ልምድ፣ በየተራው ቀን።

ብሮሹር በፍጹም በማይጠቅሳቸው ነገሮች ጀምሩ

የነዋሪውን ነጻነት የሚያሳጣ ጠበብ ያለ ቤት ከሆነ፣ ወጥቶ ለመግባት የደህንነት ስጋት ካለበት፣ ወይም መብራትና ውሃ መጣ አልመጣ እያሉ የሚጨነቁበት ከሆነ፣ ቅንጦቱ ምኑ ላይ ነው? እሁድ ጠዋት ታንኩ ባዶ ሲሆን የእብነበረድ ሎቢ አይረዳችሁም።

ሰፊ የካሬ አማራጭ፣ የማይቆራረጥ የውሃና የመብራት አቅርቦት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ ቦታ መገኘት ለእኔ አንድ መነሻ የምወስዳቸው ነገሮች ናቸው። ቅንጦቱ አይደሉም — መነሻዎቹ ናቸው። ቃሉ እንኳ ከመነሳቱ በፊት ቤት ሊኖረው የሚገባው ነገር ናቸው። ግን ብቻቸውን በቂ አይደሉም።

ከዚያ የተገነቡት ነገሮች

ከእነዚህ በሻገር የግንባታና የፊኒሺንግ ጥራት — ከአምስት ወር ሳይሆን ከአምስት ዓመት በኋላም ትክክል የሚመስል። በቂ የተፈጥሮ ብርሃን፣ ምክንያቱም ጨለማ አፓርትመንት ዋጋው ምንም ይሁን ጨለማ አፓርትመንት ነው። ከፍ ያለ ጣሪያ፣ ከማንኛውም ዕቃ በላይ ክፍል እንዴት እንደሚሰማ የሚቀይር። እና — ብዙ ጊዜ የሚረሳው — ከርክክብ በኋላ ያለው የቤቱ ጥገናና አስተዳደር፣ ምክንያቱም ሕንፃ ቁልፍ በተረከባችሁበት ቀን አይጠናቀቅም፤ ከዚያ በኋላ በየቀኑ ይተዳደራል፣ ወይም ይጎዳል።

ለምሳሌ፣ የመዋኛ ገንዳ አለው መባሉ ብቻ ቅንጡ አያሰኘውም። ለስንት ነዋሪዎች ነው? ንጽህናውስ እንዴት ይጠበቃል? የሚለው ቅንጡነቱን ይወስነዋል።

የአሜኒቲ ፈተና

ጀነሬተር አለው ማለትም ቅንጡ ነው ማለት አይደለም። የጀነሬተሩ ሀይል ምን ያህል ነው? ሊፍቱንና የኮሪደሩን መብራት — ወይስ ሙሉ አፓርትመንታችሁን? ነዋሪው የእለት ተእለት እንቅስቃሴውን ሳይስተጓጉል ኑሮውን መቀጠል ይችላል? ወይስ «ተጠባባቂ ጀነሬተር» ማለት የደበዘዘ ደረጃ መብራት ብቻ ነው?

ስለዚህ የሽያጭ ቢሮ አሜኒቲዎችን ሲዘረዝር በእያንዳንዱ ጊዜ የመከታተያ ጥያቄውን ጠይቁ፦

  • መዋኛ ገንዳ፦ ስንት ቤቶች ይጋሩታል፣ ማን ይጠብቀዋል፣ ያ ጥገና ነዋሪዎችን በወር ምን ያስከፍላል?
  • ጀነሬተር፦ ምን ያበራል፣ ለምን ያህል ጊዜ፣ ነዳጁን ማን ይከፍላል?
  • ጂም፣ አትክልት ስፍራ፣ የልጆች መጫወቻ፦ ከርክክብ በኋላ ማን ያስተዳድረዋል፣ በምን በጀት፣ በማን ውሳኔ?
  • ደህንነት፦ በር ላይ ያለ ዘበኛ ነው፣ ወይስ ሥርዓት — ካሜራ፣ የመግቢያ ቁጥጥር፣ አሠራር?

በፕላኑ ላይ ያለ ግን በየቀኑ ኑሮ ውስጥ የሌለ አሜኒቲ በብሮሹር ላይ ያለ መስመር እንጂ የቤታችሁ አካል አይደለም።

ቅንጦት ምን ማለት መሆን አለበት

ለእኔ አንድ ቤት ቅንጡ ለመባል መሰረታዊ አሜኒቲዎችን ከማቅረብ በዘለለ ኑሮአችሁን የምር አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ መሆን ይኖርበታል — እንግዶችን አፓርትመንቱን በምታሳዩበት ቀን ብቻ ሳይሆን፣ በማክሰኞ ምሽት የሚሰማችሁ ዓይነት ልዩነት።

ለእናንተስ አንድ ቤት ቅንጡ የሚሆነው ምን ሲኖረው ነው?

ጥያቄ አለዎት? የመጀመሪያው ንግግር ነፃ ነው — ሠላሳ ደቂቃ፣ በሚመችዎ ቋንቋ።

ቀጠሮ ይያዙ